Welcome to the

Ethiopia
Space shortcuts
Ethiopia ET
Skip to end of metadata
Go to start of metadata

በተሁለደሬ ወረዳ 012 ጎበያ ቀበሌ የስነ-ምግብ ተኮር ግብርናን ተግባራዊ ለማድረግ በ ISD (በዘላቂ ልማት መካነ ጥናት ፕሮጀክት) የተለዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ ወረዳ በ012 ጎበያ ቀበሌ የስነ-ምግብ ተኮር ግብርናን ተግባዊ ለማድረግ በደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና በዘላቂ ልማት መካነ ጥናት ትብብር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተገልጿል፡፡
በ012 ጎበያ ቀበሌ የስነ-ምግብ ተኮር ግብርናን ለማስፋፋት በደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በ ISD (በዘላቂ ልማት መካነ ጥናት ፕሮጀክት) ትብብር ለመስኖ ማህበር አባል አርሶ አደሮች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ላይ በተፈጥሮ ግብርና ውጤታማ የሆኑ አርሶ አደሮች ተሞክሮአቸውን አቅርበዋል፡፡
ወጣት ሁሴን መስፍንና አርሶ አደር ከበደ ሰይድ እንዳሉት በተፈጥሮ ግብርና በትንሹ ማሳ ላይ ብዙ አትክልቶችን በስብጥር በመጠቀም ብዙ ምርት እንዳገኙና ጤንነታቸውም የተጠበቀ እንድሆንና መቀጨርን ለመከላከል ስለጠቀመን ሌሎች አርሶ አደሮች የኛን ተሞክሮ በማስፋፋት በተፈጥሮ ግብርና ተጠቃሚ እንድሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርት እና የበዘላቂ ልማት መካነ ጥናት ፕሮጀክት አስተባባሪ ሲስተር ዘነበች ቆርቾ እንደገለጹት በዘላቂ ልማት መካነ ጥናት ትብብር የስነ ምግብ ተኮር ግብርና ለማስፋፋት የተሌዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀው የገበያ ትስስር መፈጠር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ሲስተር ዘነበች አክላለውም በተፈጥሮ ግብርና የግብርና ምርትን ከሰው ሰራሽ ኬሚካሎች ነጻ በሆነ ተፈጥሮን ወይም ስነ-ምህዳርን መሰረት አድርጎ የሚመረትበት ዘዴ በመሆኑ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በመጨመር የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ፣ ተገቢ ያልሆነ ወጭ እንዳይወጣ፣ ስነምህዳሩን በመጠቀም ብዝሀ ሕይወት እንድጨምር እና ዘላቂ ልማትን የሚረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
“የተፈጥሮ ግብርና የሀገራችንን አረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕቅድ ለማሳካት አስተዋጽኦ ያበረክታል”!




  • No labels
Ethiopia ET